Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ ‘መሬት ለዘለቄታ አይሸጥ፤ ምክንያቱም ምድሪቱ የእኔ ናት፤ እናንተም መጻተኞችና እንግዶች ናችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ምድሪቱም የእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድሪቱን ለዘለዓለም አትሽጧት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ምድሪቱ ለዘለቄታ መሸጥ አይገባትም፤ እርስዋ የእኔ እንጂ የእናንተ አይደለችም፤ እናንተ እንደ መጻተኛ ሆናችሁ እንድትጠቀሙባት ብቻ ፈቅጃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “ምድ​ርም ለእኔ ናትና፥ እና​ን​ተም በእኔ ፊት እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች ናች​ሁና ምድ​ርን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ሽጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ምድርም ለእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:23
22 交叉引用  

“እኔ ለአገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ሆኜ በመካከላችሁ የምኖር ነኝና ለመቃብር የምትሆን ቦታ ሽጡልኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።”


ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።


ናቡቴ ግን አክዓብን፣ “ዐፅመ ርስቴን እለቅቅልህ ዘንድ እግዚአብሔር አይበለው” ሲል መለሰለት።


እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ቢስም ነው።


በዚያ ጊዜ እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድሬ እነቅላቸዋለሁ፤ ለስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በሕዝቦችም ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ አደርገዋለሁ።


እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ፤ ትእዛዞችህን ከእኔ አትሰውር።


ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤


“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴን አድምጥ፤ ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤ በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ።


ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣ ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።”


እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።


አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣


ሲፓራም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ሲል የልጁን ስም ጌርሳም ብሎ ጠራው።


እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”


ከዚህ ላይ መሸጥ ወይም መለወጥ የለባቸውም። ይህ ከምድሪቱ ሁሉ ምርጥ ስለ ሆነ፣ ወደ ሌላ እጅ አይተላለፍም፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና።


በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፤ የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።


እነሆ፤ እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ይቀናል፤ ስለ ሕዝቡም ይራራል።


አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣ በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤ ምድሬን ከፋፍለዋል፤ ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።


ዐምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱ ሁሉ ላሉ ነዋሪዎች በሙሉ ነጻነት ዐውጁ፤ ይህም ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደ ቤተ ሰቡ ርስት፣ ወደ ወገኑም ይመለስ።


ርስት አድርጋችሁ በምትይዙት ምድር ሁሉ መሬት የሚዋጅበት ሁኔታ እንዲኖር አድርጉ።


አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።


ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告