Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 23:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 እነዚህ መሥዋዕቶች ለእግዚአብሔር ሰንበት ከምታቀርቡት፣ ከስጦታችሁ፣ ከስእለታችሁና ከበጎ ፈቃድ ስጦታችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ስጦታዎች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 እነዚህም ከጌታ ሰንበታት ሌላ፥ ለጌታም ከምትሰጡት ከስጦታችሁ ሌላ፥ ከስእለታችሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈቃዳችሁም ከምታቀርቡአቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እነዚህም በዓላት ከእግዚአብሔር ሰንበቶች ጋር ተጨማሪ ሆነው የሚከበሩ ናቸው፤ ለእግዚአብሔር ከምትሰጡት ስጦታ ስእለት ሲፈጸምላችሁ ከምትሰጡት ስጦታና በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት ሁሉ ጋር ተደምረው የሚቀርቡ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እነ​ዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ታት ሌላ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ት​ሰ​ጡት ከስ​ጦ​ታ​ችሁ ሌላ፥ ከስ​እ​ለ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ከም​ታ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 እነዚህም ከእግዚአብሔር ሰንበታት ሌላ፥ ለእግዚአብሔርም ከምትሰጡት ከስጦታችሁ ሌላ፥ ከስእለታችሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈቃዳችሁም ከምታቀርቡአቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 23:38
15 交叉引用  

የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው የሌዋዊው የዪምና ልጅ ቆሬ ደግሞ ለእግዚአብሔር በቀረበው የበጎ ፈቃድ ስጦታ ላይ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትንም ነገሮች ለማከፋፈል፣ ኀላፊ ነበረ።


በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለስ ዘንድ፣ ነፍሴን ከሞት፣ እግሬንም ከመሰናክል አድነሃልና።


እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል፤ በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ነው።


“ ‘ገዥው የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፣ በምሥራቅ ትይዩ የሆነው በር ይከፈትለት፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕቱንም ሆነ የኅብረት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይወጣል፤ በሩም ይዘጋል።


“ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


“ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።


“ ‘የሚቃጠል መሥዋዕትንና የእህል ቍርባንን፣ መሥዋዕትንና የመጠጥ ቍርባንን በተመደበላቸው ቀን ለእግዚአብሔር በእሳት ለማቅረብ፣ የተቀደሱ ጉባኤዎችን የምታውጁባቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።


“ ‘የምድራችሁን ፍሬ ከሰበሰባችሁ በኋላ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ጀምራችሁ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር በዓል አክብሩ፤ የመጀመሪያው ቀን የዕረፍት ዕለት ነው፤ ስምንተኛውም ቀን እንደዚሁ የዕረፍት ዕለት ይሆናል።


“ ‘ከስእለትና ከበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በበዓላታችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።’ ”


ወደዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ ስእለቶቻችሁንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፣ የቀንድ ከብት መንጋችሁን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አምጡ።


跟着我们:

广告


广告