Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 22:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የበሬው ወይም የበጉ የአካሉ ክፍል ረጅም ወይም አጭር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አካሉ የጐደለ ወይም ቅርጹ የተበላሸ እንስሳ የበጎ ፈቃድ መሥዋዕት ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፤ ነገር ግን ስእለት የተፈጸመለት ሰው መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በሬው ወይም በጉ የተጨመረበት ወይም የጐደለበት ነገር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 22:23
7 交叉引用  

ፈቃደኛ የሆኑ እስራኤላውያን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲያከናውኑት ላዘዛቸው ሥራ ሁሉ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎችን ለእግዚአብሔር አመጡ።


ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ።


ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም ማንኛውንም ዐይነት እከክ ወይም ቋቍቻ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ ከእነዚህ መካከል የትኛውንም በመሠዊያው ላይ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ።


አባለዘሩ የተቀጠቀጠ ወይም የተኰላሸ፣ የተሰነጠቀ ወይም የተቈረጠ ማንኛውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ እነዚህንም በምድራችሁ አትሠዉ።


የታወረውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፣ ያ በደል አይደለምን? ዐንካሳውን ወይም በሽተኛውን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ያስ በደል አይደለምን? ያንኑ ለገዣችሁ ብታቀርቡ፣ በእናንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ይቀበለዋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፣ ዐንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማንኛውም ዐይነት ከባድ ጕድለት ያለበት ከሆነ፣ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤


እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።


跟着我们:

广告


广告