Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 22:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም ማንኛውንም ዐይነት እከክ ወይም ቋቍቻ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ ከእነዚህ መካከል የትኛውንም በመሠዊያው ላይ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዓይነ ስውር ወይም የተሰበረ ወይም አካለ ጎዶሎ ወይም የሚመግል ቁስል ወይም የእከክ ደዌ ያለበት ወይም ቋቁቻ የወጣበት ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለጌታ አታቅርቡ፤ እነርሱንም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ በመሠዊያው ላይ ለጌታ አትሠዉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዕውር፥ ሰባራ ወይም ጉንድሽ የሆነ ወይም የሚመግል ቊስል፥ እከክ ወይም ሽፍታ ያለበት ማናቸውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዕውር፥ ወይም ሰባራ፥ ወይም ምላሱ የተ​ቈ​ረጠ፥ ወይም የሚ​መ​ግል ቍስል ያለ​በት፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለእ​ሳት ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር አታ​ሳ​ርጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበት ወይም እከካም ወይም ቍቍቻም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ እነዚህም ለእሳት ቍርባን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር አታሳርጉ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 22:22
9 交叉引用  

አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑ መባውን ሁሉ አምጥቶ በመሠዊያው ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።


አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መባውን ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።


እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ፤ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት አይኖረውምና።


ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት ሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና እንከን የሌለበትን ያቅርብ።


አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም።


ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣


የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።


የታወረውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፣ ያ በደል አይደለምን? ዐንካሳውን ወይም በሽተኛውን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ያስ በደል አይደለምን? ያንኑ ለገዣችሁ ብታቀርቡ፣ በእናንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ይቀበለዋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告