Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 22:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡትን የተቀደሰ መሥዋዕት ካህናቱ አያርክሱት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ካህናቱ የእስራኤል ልጆች ለጌታ የሚያቀርቡትን የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር የሚያመጡአቸውን የተቀደሱ ስጦታዎች፥ ካህናት ማርከስ የለባቸውም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አያ​ር​ክሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15-16 የምቀድሳቸውም እግዚአብሔር እኔ ነኝና ከተቀደሰው በበሉ ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡትን በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 22:15
6 交叉引用  

አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።


ካህናቷ በሕጌ ላይ ያምፃሉ፤ ንዋያተ ቅድሳቴን ያረክሳሉ፤ የተቀደሰውን ከረከሰው አይለዩም፤ በጐደፈውና በንጹሑ መካከል ልዩነት እንደሌለ ያስተምራሉ፤ ሰንበታቴን ከማክበር ዘወር ብለዋል፤ በዚህም በመካከላቸው ተንቄአለሁ።


ከመሥዋዕቱ የሚበላ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሷልና ይጠየቅበታል፤ ያም ሰው ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ።


ይህንኑ የተቀደሰ መሥዋዕት እንዲበሉና ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽሙ አያድርጉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”


“ ‘ካህናት ትእዛዞቼን በመናቅ በደለኛ እንዳይሆኑና እንዳይሞቱ ይጠብቋቸው፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


የተመረጠውን ክፍል ካቀረባችሁ በዚህ በደለኞች አትሆኑም፤ ደግሞም የተቀደሰውን የእስራኤላውያንን መባ አታረክሱም፤ አትሞቱምም።’ ”


跟着我们:

广告


广告