Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 19:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ ‘እንዳትረክሱባቸው ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር አትበሉ፤ መናፍስት ጠሪዎችንም አትፈልጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 “ወደ ሙታን መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ አትፈልጉአቸው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “ከሙታን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ከጠንቋዮች ምክር አትጠይቁ፥ ይህን ብታደርጉ የረከሳችሁ ትሆናላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 “ወደ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ችና ወደ ጠን​ቋ​ዮች አት​ሂዱ፤ እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ሱ​ባ​ቸ​ውም አት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቍዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 19:31
22 交叉引用  

እንዲሁም ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። ጥንቈላና መተት አደረጉ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ፤ ለቍጣም አነሣሡት።


የገዛ ወንድ ልጁን በእሳት ሠዋ፤ አስማት፣ መተትና ጥንቈላ አደረገ፤ ሙታን ጠሪዎችንና መናፍስት ሳቢዎችን ጠየቀ። ለቍጣ ያነሣሣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።


ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤


እርሱም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ወንዶች ልጆቹን በእሳት ሠዋ፤ ሟርት፣ አስማት፣ መተትና ጥንቈላ አደረገ፤ ሙታን ጠሪዎችንና መናፍስት ሳቢዎችን ጠየቀ። ለቍጣ ያነሣሣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


“መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።


ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጕተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።


የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል! እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስኪ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስኪ ያድኑሽ።


ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?


“ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ። “ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።


“ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


“ ‘ከመካከላችሁ ሙታን ጠሪ ወይም መናፍስት ጠሪ የሆነ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ይገደል፤ በድንጋይም ይወገሩ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’ ”


ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በጥንቈላ ሥራው ስላስገረማቸውም ትኵረት ሰጥተው ይከተሉት ነበር።


ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣


ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በአርማቴም አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦል ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባርሯቸው ነበር።


跟着我们:

广告


广告