Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 18:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እናንተም ምድሪቱን ብታረክሷት፣ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም ትተፋችኋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ያለዚያ ግን ምድሪቱን ካረከሳችሁ እርሷ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ አንቅራ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም አንቅራ ትተፋችኋለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ምድሪቱን ብታረክስዋት ከእናንተ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች እንደ ተፋች እናንተንም አንቅራ ትተፋችኋለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ምድ​ሪ​ቱም ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን ሕዝብ እንደ ተፋች ባረ​ከ​ሳ​ች​ኋት ጊዜ እና​ን​ተ​ንም እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ምድሪቱም ረክሳለችና፤ ባረከሳችኋት ጊዜ ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እናንተን እንዳትተፋችሁ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 18:28
9 交叉引用  

እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቷል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሕዝቡ እናንተን፣ “ሰዎችን ቦጫጭቀው ይበላሉ፤ ሕዝብንም ልጅ አልባ ያደርጋሉ” ስላሏችሁ፣


“የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ሕዝብ በገዛ ምድራቸው ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በሥራቸውና በአኗኗራቸው አረከሷት፤ ጠባያቸውም በፊቴ፣ ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ዐይነት ነበር።


ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው።


ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች።


“ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ።


“ ‘እንድትኖሩባት እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ አድርጉም።


እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።


እንግዲህ ለብ ያልህ ብቻ እንጂ ትኵስ ወይም ቀዝቃዛ ስላልሆንህ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው።


跟着我们:

广告


广告