ዘሌዋውያን 18:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከእናትና ከሴት ልጅዋ፥ እንዲሁም ከልጅ ልጆችዋ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ፤ እነርሱም የቅርብ ዘመዶችህ ስለ ሆኑ ኃጢአት ይሆንብሃል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 የሴትንና የሴት ልጅዋን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው። 参见章节 |