Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 16:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ይለብሳል፤ ወጥቶም ለእርሱ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት እና ለሕዝቡ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በተቀደሰውም ቦታ ሰውነቱን ታጥቦ የዘወትር ልብሱን ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱንና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቅርብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍራ ገላ​ውን በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ሌላ​ው​ንም ልብስ ለብሶ ይወ​ጣል፤ የእ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ለካ​ህ​ናቱ እን​ዳ​ስ​ተ​ሰ​ረየ ለራ​ሱም፥ ለሕ​ዝ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የሕዝቡንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 16:24
14 交叉引用  

የአሮን ወንድ ልጆች ክብርና ማዕርግ እንዲኖራቸው ሸሚዞችን፣ መታጠቂያዎችን፣ የራስ ማሰሪያዎችን አብጅላቸው።


እነዚህን ልብሶች ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ካለበስህ በኋላ ቅባቸው፤ ካናቸው፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ቀድሳቸው።


ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”


በሰባተኛውም ቀን ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ራሱን፣ ጢሙን፣ ቅንድቡንና ሌላውንም ጠጕር ሁሉ ይላጭ። ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።


የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።


እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ነገር የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ሰውነቱንም በውሃ ካልታጠበ፣ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ።


ሙሴ አሮንን፣ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአት መሥዋዕትህንና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት የሕዝቡን መሥዋዕት አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው።


እነዚህ ሁሉ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ በምግብና በመጠጥ እንዲሁም የተለያዩ በመታጠብ የሚደረጉ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告