ዘሌዋውያን 14:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ካህኑ የተበከሉት ድንጋዮች ተሰርስረው እንዲወጡና ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲጣሉ ይዘዝ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 የሻጋታው ምልክት ያለባቸው ድንጋዮች ተፈልፍለው ወጥተው ከከተማው ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ እንዲጣሉ ይዘዝ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ወደ ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ወደ ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። 参见章节 |