Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 14:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ካህኑም የኀጢአት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከርኩሰቱ ለሚነጻውም ሰው ያስተስርይለት፤ ከዚህ በኋላ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ይረድ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ካህኑም የኃጢአቱን መሥዋዕት ያቀርባል፥ ከርኩሰቱም ለሚነጻው ሰው ያስተሰርይለታል፤ ከዚያም በኋላ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያርዳል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ከዚህም በኋላ ካህኑ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት በማቅረብ የመንጻትን ሥርዓት ይፈጽማል፤ ቀጥሎም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርበውን እንስሳ ያርዳል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ ለማ​ን​ጻት ለሚ​ነ​ጻው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከዚ​ህም በኋላ ካህኑ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም የኃጢአቱን መሥዋዕት ያቀርባል፥ ከርኩሰቱም ለሚነጻው ሰው ያስተሰርይለታል፤ በኋላም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያርዳል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 14:19
8 交叉引用  

“ካህኑም ከተባዕቱ ጠቦቶች በመውሰድ ከሎግ ዘይቱ ጋራ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዛቸው።


ካህኑ ከበደል መሥዋዕቱ ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ታችኛውን ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ።


ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሹ በእግዚአብሔር ፊት ለሰውየው ያስተሰርይለታል።


“ ‘አንድ ሰው ስላየውና ስለሚያውቀው ነገር ሕጋዊ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ተጠይቆ ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆን፣ ይህ ሰው ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል።


ስለ ኀጢአቱም ቅጣት የኀጢአት መሥዋዕት እንድትሆነው ከመንጋው አንዲት የበግ ወይም የፍየል እንስት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ ካህኑም ስለ ኀጢአቱ ያስተሰርይለታል።


ሕግ ከሥጋ ባሕርይ የተነሣ ደክሞ ሊፈጽም ያልቻለውን፣ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኀጢአተኛ ሰው አምሳል፣ የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆን በመላክ ፈጸመው፤ በዚህም ኀጢአትን በሥጋ ኰነነ፤


እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።


跟着我们:

广告


广告