Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ በሽተኛውን ይመርምረው፤ ቍስሉ ለውጥ ካላመጣና በቈዳውም ላይ ካልተስፋፋ እንደ ገና ሰባት ቀን ያግልለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው መገታቱን ቢያይ፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ፥ አሁንም ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ካህኑ በሰባተኛው ቀን እንደገና ይመርምረው፤ በሚመረምረውም ጊዜ ቊስሉ ምንም ለውጥ ሳያሳይ እንደ ነበረ ሳይስፋፋ ቢያገኘው፥ አሁንም ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ካህኑ ያችን ደዌ ይያት፤ እነ​ሆም፥ ያች ደዌ በፊት እንደ ነበ​ረች ብት​ሆን፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባት​ሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው በዓይኑ ፊት እንደ ነበረ ቢሆን፥ በቁርበቱም ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይዘጋበታል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:5
4 交叉引用  

ካህን በመሆን እርሱን የሚተካውና በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚመጣው ወንድ ልጅ ሰባት ቀን ይለብሳቸዋል።


በቈዳው ላይ ያለው ቋቍቻ ነጭ ሆኖ ቢታይ፣ ነገር ግን ከቈዳው በታች ዘልቆ ባይገባና በቦታው ላይ የሚገኘው ጠጕር ወደ ነጭነት ባይለወጥ፣ ካህኑ በሽተኛውን ሰባት ቀን ያግልለው።


በሰባተኛው ቀን ካህኑ እንደ ገና ይመርምረው፤ ቍስሉ ከከሰመና በቈዳው ላይ ካልተስፋፋ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ቍስሉ ችፍታ እንጂ ሌላ አይደለም። ሰውየው ልብሱን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።


“የሚነጻው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ በሥርዐቱም መሠረት ንጹሕ ይሆናል። ከዚህም በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል፤ ነገር ግን ሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቈይ።


跟着我们:

广告


广告