Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ካህኑ በሰባተኛው ቀን የሚያሳክከውን የሰውየውን ቍስል ይመርምር፤ በቈዳው ላይ ካልሰፋና ከቈዳው በታች ዘልቆ ካልገባ ካህኑ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ልብሱን ዐጥቦ ንጹሕ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በሰባተኛውም ቀን እንደገና ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ ቊስሉ በመስፋፋት ላይ ካልተገኘና በዙሪያውም ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ የጐደጐደ ካልሆነ ያ ሰው የነጻ መሆኑን ያስታውቅለት፤ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ቈረ​ቈ​ሩን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ከተ​ላጨ በኋላ ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ባይ​ሰፋ፥ መል​ኩም ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል፤ ልብ​ሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ባይሰፋ፥ መልኩም ወደ ቁርበቱ ባይጠልቅ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:34
6 交叉引用  

ካህኑ ቍስሉን ይመርምር፤ ከቈዳው በታች ዘልቆ ከገባ፣ በውስጡም ያለው ጠጕር ቢጫና ቀጭን ከሆነ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ የሚያሳክክ የራስ ወይም የአገጭ ተላላፊ በሽታ ነው።


ከቈሰለው ቦታ በቀር ጠጕሩን ይላጭ፤ ካህኑ ሰባት ተጨማሪ ቀን ሰውየውን ያግልል።


ንጹሕ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ ግን የሚያሳክከው ቍስል ተስፋፍቶ ቢገኝ፣


ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


ተጠራጣሪ ለሆኑት ራሩላቸው፤


ሥራህን፣ ጥረትህንና ትዕግሥትህን ዐውቃለሁ። ክፉዎችንም ችላ ብለህ እንዳላለፍሃቸው፣ ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትንም መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው ዐውቃለሁ።


跟着我们:

广告


广告