Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 12:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ ‘ሴትዮዋ ወንድ ወይም ሴት ልጅዋን ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲፈጸም፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት የአንድ ዓመት ጠቦት፣ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ የዋኖስ ጫጩት ወይም አንድ ርግብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወስዳ ካህኑ ዘንድ ታቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣለት።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 12:6
15 交叉引用  

እግዚአብሔርም “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንድ ፍየልና አንድ በግ፣ በተጨማሪም አንድ ዋኖስና አንድ ርግብ ዐብረህ አቅርብልኝ” አለው።


“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ሴት አርግዛ ወንድ ልጅ በምትወልድበት ጊዜ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ትረክሳለች።


ነገር ግን የወለደችው ሴት ልጅ ከሆነ፣ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ ሁለት ሳምንት ትረክሳለች፤ ከዚያም ከደሟ እስክትነጻ ስድሳ ስድስት ቀን ትቈይ።


ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያቅርበው፤ ያስተስርይላትም፤ ሴትዮዋም ከደሟ ፈሳሽ ትነጻለች። “ ‘ሴትዮዋ ወንድ ወይም ሴት ብትወልድ ሕጉ ይኸው ነው።


እንዲሁም ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ዐቅሙ የፈቀደውን አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ።


በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዞ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ።


በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዛ በመቅረብ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ትሰጣለች።


በስምንተኛው ቀን ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ይዞ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ዘንድ ያምጣ።


በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻታቸው ወቅት በተፈጸመ ጊዜ፣ ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ለጌታ ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ወጡ፤


ዮሐንስ በማግስቱም፣ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፤


እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።


እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።


跟着我们:

广告


广告