Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 10:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት ያንተና የልጆችህ ድርሻ ይህ ስለ ሆነ፣ በተቀደሰ ስፍራ ብሉት፤ እንዲህ ታዝዣለሁና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለጌታም ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ድርሻ ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም እንዲህ ታዝዣለሁና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የምግብ መባ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ የተመደበ ድርሻ ስለ ሆነ በተቀደሰ ስፍራ ብሉት። ይህን እንድታደርጉ እግዚአብሔር አዞኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አዝ​ዞ​ኛ​ልና፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን ለአ​ን​ተም፥ ለል​ጆ​ች​ህም የተ​ሰጠ ሥር​ዐት ነውና በቅ​ዱስ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ሥርዓት ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 10:13
7 交叉引用  

ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና።


ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ቂጣ ጋግሩ፤ እጅግ ቅዱስ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።


ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የእናንተ ድርሻ ሆኖ ስለ ተሰጠ፣ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ብሉት።


የተረፈውም የእህሉ ቍርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ቍርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።


የተረፈውንም አሮንና ልጆቹ ይብሉት፤ ቂጣውን በተቀደሰው ስፍራ፣ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ አደባባዩ ላይ ይብሉት።


እጅግ ቅዱስ መሆኑን በማሰብ በተቀደሰ ስፍራ ብላው፤ እያንዳንዱም ወንድ ከዚሁ ይብላ፤ ይህ ለአንተም የተቀደሰ ነው።


የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ስጦታ ለካህኑ ይሆናል፤ ለካህኑ የሚሰጠውም ሁሉ የራሱ ይሆናል።’ ”


跟着我们:

广告


广告