ዘሌዋውያን 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መባውን ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ያም ሰው የእንስሳውን ሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መሥዋዕቱን በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። 参见章节 |