Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 1:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ከከፍታ ስፍራ እሳትን ላከ፤ ወደ ታች ወደ ዐጥንቶቼም ሰደደው፤ በእግሮቼ ላይ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም ጣለኝ፤ ቀኑን ሙሉ በማድከም፣ ባዶ አድርጎ አስቀመጠኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሜም። ከላይ እሳ​ትን ሰደደ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም አቃ​ጠለ፤ ለእ​ግሬ ወጥ​መድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለ​ሰኝ፥ አጠ​ፋ​ኝም፤ ቀኑ​ንም ሁሉ መከራ አጸ​ና​ብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 1:13
31 交叉引用  

እግሩ በወጥመድ ይያዛል፤ በመረብም ይተበተባል።


እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣ በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ።


ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።


ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


ትዕቢተኞች ወጥመድ በስውር አስቀመጡብኝ፤ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ፤ በመንገዴም ላይ አሽክላ አኖሩ። ሴላ


እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።


ሕይወቴ በመጨነቅ፣ ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ ከመከራዬ የተነሣ ጕልበት ከዳኝ፤ ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።


ሕይወቴን የሚፈልጓት፣ ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤ እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።


ወደ ወጥመድ አገባኸን፤ በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።


ጥሬውን ሥጋ ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ነገር ግን ጭንቅላቱን፣ እግሮቹንና ሆድ ዕቃውን በእሳት ላይ ጠብሳችሁ ብሉት።


በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።


ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ነደደ፤ ዛሬ እንደሚታዩትም ማንም የማይኖርባቸው ፍርስራሾች አደረጋቸው።


“ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግህብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቷል፤ ልቤም ደክሟል።”


ከመንገድ ጐትቶ አስወጣኝ፤ ቈራረጠኝም፤ ያለ ረዳትም ተወኝ።


ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤


መረቤን በርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ነገር ግን እርሷን ሳያያት በዚያ ይሞታል።


መረቤን በላዩ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል። ወደ ባቢሎን እወስደዋለሁ፤ በእኔ ላይ ስላመፀም በዚያ እፈርድበታለሁ።


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ብዙ ሕዝብ ይዤ፣ መረቤን በላይህ ላይ እጥላለሁ፤ በመረቤም ጐትተው ያወጡሃል።


ሲበርሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ። ስለ ክፉ ሥራቸውም፣ በጉባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።


ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።


እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፣ በናፍቆት የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቈርጥ ልብ ይሰጥሃል።


በዚያ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችንም ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል።


“አምላካችን የሚባላ እሳት ነውና።”


跟着我们:

广告


广告