Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:53 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 አንዲት ሴት ከላይ የወፍጮ መጅ በአቢሜሌክ ራስ ላይ ለቀቀችበት፤ ጭንቅላቱንም አፈረሰችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 አንዲት ሴት ከላይ የወፍጮ መጅ በራሱ ላይ ለቀቀችበት፤ ጭንቅላቱንም አፈረሰችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 ነገር ግን አንዲት ሴት በራሱ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል አናቱን ፈጠፈጠችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 አን​ዲ​ትም ሴት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ራስ ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጣለ​ች​በት፤ አና​ቱ​ንም ሰበ​ረ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 አንዲትም ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፥ አናቱንም ሰበረችው።

参见章节 复制




መሳፍንት 9:53
9 交叉引用  

የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”


ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፣ የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቷል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፣ “የሰውየው ራስ ተቈርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው።


ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?


ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ ያቀደውን፣ በቴማን በሚኖሩትም ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤ ታናናሹ መንጋ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።


ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደውን፣ በባቢሎናውያንም ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤ ከመንጋው ታናናሹ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።


ዲቦራ መልሳ፣ “ይሁን ዕሺ፤ መሄዱን ዐብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባርቅ ጋራ ወደ ቃዴስ ሄደች፤


“የእሾኽ ቍጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቍጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ!’ አላቸው።


ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።”


አቢሜሌክም ተዋግቶ ግንቡን ያዘ፤ ይሁን እንጂ እሳት ለመለኰስ ወደ ግንቡ መግቢያ አጠገብ እንደ ደረሰ፣


跟着我们:

广告


广告