Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እርሱም ሰዎቹን አስከትሎ ወጣ፤ ከዚያም ሰዎቹን ሦስት ቦታ መድቦ በዕርሻዎቹ ውስጥ አድፍጠው እንዲጠባበቁ አደረገ። አቢሜሌክ የሴኬም ሰዎች ከከተማዪቱ መውጣታቸውን እንዳየም ካደፈጠበት ሊወጋቸው ተነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 እርሱም ሰዎቹን አስከትሎ ወጣ፤ ከዚያም ሰዎቹን ሦስት ቦታ መድቦ በዕርሻዎቹ ውስጥ አድፍጠው እንዲጠባበቁ አደረገ። አቤሜሌክ የሴኬም ሰዎች ከከተማይቱ መውጣታቸውን እንዳየም ካደፈጠበት ሊወጋቸው ተነሣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 የእርሱ ተከታዮች የሆኑትን ሰዎች ወስዶ በሦስት ወገን በመክፈል በየመስኩ ሸምቀው እንዲጠባበቁ አደረገ፤ ሴኬማውያንንም ከከተማ ሲወጡ ባየ ጊዜ እነርሱን ከሸመቀበት ቦታ ወጥቶ ገደላቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ሕዝ​ቡ​ንም ወስዶ በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሜ​ዳም ሸመቀ፤ ተመ​ለ​ከ​ተም፤ እነ​ሆም፥ ሕዝቡ ከከ​ተማ ወጡ፤ ተነ​ሣ​ባ​ቸ​ውም፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ሕዝቡንም ወስዶ በሦስት ወገን ከፈላቸው፥ በሜዳም ሸመቀ፥ ተመለከተም፥ እነሆም፥ ሕዝቡ ከከተማ ወጡ፥ ተነሣባቸውም መታቸውም።

参见章节 复制




መሳፍንት 9:43
4 交叉引用  

ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጋታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም ዐብሬአችሁ በርግጥ እወጣለሁ” አላቸው።


በማግስቱም የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቢሜሌክ ተነገረው፤


ከዚያም አቢሜሌክና ዐብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፣ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው።


በማግስቱም ሳኦል ሰራዊቱን ከሦስት ቦታ ከፈለው፤ ሊነጋጋ ሲል፣ የአሞናውያንን ሰፈር ጥሰው በመግባት ፀሓይ ሞቅ እስኪል ድረስ ፈጇቸው። በሕይወት የተረፉትም ሁለት እንኳ ሆነው በአንድ ላይ ሊሆኑ እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።


跟着我们:

广告


广告