መሳፍንት 9:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩባኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቢሜሌክ እንገዛለን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቤሜሌክ እንገዛለን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 የአቤድም ልጅ ገዓል፥ “አቤሜሌክ ማን ነው? እንገዛለትስ ዘንድ የሴኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ጠባቂ አይደለምን? ከሴኬም አባት ከኤሞር ሰዎች ጋርስ አገልጋዩ አይደለምን? ስለምንስ ለዚህ እንገዛለን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 የአቤድም ልጅ ገዓል፦ የምንገዛለት አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድር ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልም የእርሱ ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፥ 参见章节 |