Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሰራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሠራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ ጌዴዎን በበረሓው መንገድ አድርጎ በኖባሕና በዮግበሃ ምሥራቅ በኩል ወጣና የጠላት ሠራዊት ሳያስበው በመዝናናት ላይ እያለ አደጋ ጣለበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጌዴ​ዎ​ንም በድ​ን​ኳን የሚ​ኖሩ ሰዎች ባሉ​በት መን​ገድ በኖ​ቤ​ትና በዮ​ግ​ቤል በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ተዘ​ልሎ ሳለ አጠ​ፋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጌዴዎንም የድንኳን ተቀማጮች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ በምሥራቅ በኩል ወጣ፥ ሠራዊቱም ተዘልሎ ነበርና ሠራዊቱን መታ።

参见章节 复制




መሳፍንት 8:11
8 交叉引用  

ዓጥሮትሾፋንን፣ ኢያዜርን፣ ዮግብሃን፣


እንዲሁም ኖባህ ቄናትንና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ በራሱ ስም፣ ኖባህ ብሎ ጠራቸው።


ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፣ በሰላምና ያለ ሥጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሏት።


በዚህ ጊዜ ዛብሄልና ስልማና ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ከሆነ ሰራዊታቸው ጋራ ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺሕ ሰይፍ ታጣቂ ሰራዊት የተረፈው ነበር።


ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ስልማና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳድዶ ያዛቸው፤ መላ ሰራዊታቸውንም እጅግ በታተነው።


ከዚያም ሳሙኤል፣ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግንም በሰንሰለት ተይዞ፣ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን?” በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።


ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፣ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፣ ይጠጡና ይዘፍኑ፣ ይጨፍሩም ነበር።


跟着我们:

广告


广告