Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እለይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋራ ይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ ይሄዳል፤ ነገር ግን፣ ‘ይህ ከአንተ ጋራ አይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ አይሄድም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እጸልይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን፥ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር አይሄድም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “አሁንም ገና ብዙ ሠራዊት አሉህ፤ እነርሱን ወደ ወንዝ ውሰዳቸውና በዚያ እኔ እፈትናቸዋለሁ፤ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው ሰው ይሂድ፤ ይቅር የምለው ሰው ደግሞ ይመለስ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አው​ር​ዳ​ቸው፤ በዚ​ያም እፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ የም​ለው እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር አይ​ሂድ የም​ለው እርሱ አይ​ሄ​ድም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፥ ወደ ውኃ አውርዳቸው፥ በዚያም እፈትናቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ የምለው እርሱ አይሄድም አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:4
10 交叉引用  

ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ።


ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።


ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።


አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤ እንደ ብርም አነጠርኸን።


ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና።


ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዟቸው ወረደ፤ እዚያም እግዚአብሔር፣ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፣ በምላሳቸው የሚጠጡትን፣ በጕልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው።


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና፤ ወደነዚያ ሸለፈታሞች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን እግዚአብሔርን የሚያግደው የለምና” አለው።


እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፣ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


跟着我们:

广告


广告