Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍችውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፣ “እግዚአብሔር የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷልና ተነሡ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍቺውን በሰማ ጊዜ ለጌታ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፥ “ጌታ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ!” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ጌዴዎን ስለ ሰውየው ሕልምና ስለ ፍቹም ምንነት በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤላውያንም ሰፈር ተመልሶ “እግዚአብሔር በምድያማውያንና በሠራዊቱ ላይ ድልን የሚያቀዳጃችሁ ስለ ሆነ ተነሡ!” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፥ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፦ እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ አለ።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:15
15 交叉引用  

ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።


እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጕምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስኪ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።


ሁለታችንም በአንዲት ሌሊት የተለያየ ሕልም አየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የየራሱ ትርጕም ነበረው።


እርሱም፣ “ጠላታችሁን ሞዓብን እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ስለ ሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን መልካዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ።


በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባርቅን፣ “ተነሣ! እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ እግዚአብሔር በፊትህ ቀድሞ ወጥቷል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺሕ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ።


የሚሉትንም ስማ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ።” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ።


ጓደኛውም መልሶ፣ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው።


ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፣ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።


ጌዴዎንም መልሶ፣ “ደኅና፤ እግዚአብሔር ዛብሄልንና ስልማናን በእጄ አሳልፎ በሚሰጥበት ጊዜ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ ሥጋችሁን እተለትላለሁ” አላቸው።


ስለዚህ እኔም ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገደ።


የፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ሰዎችም፣ “ኑ ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገር እናሳያችሁ” ሲሉ በዮናታንና በጋሻ ጃግሬው ላይ ጮኹባቸው። ስለዚህ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፣ “ተከትለኸኝ ውጣ፤ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና” አለው።


跟着我们:

广告


广告