Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን፣ ከርሱም ጋራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጧት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተሰሜን በኩል፣ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፥ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፥ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:1
14 交叉引用  

አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያ ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር።


በማግስቱም ጧት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይሥሐቅን ይዞ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጕዞውን ጀመረ፤


አሮዳዊው ሣማ፣ አሮዳዊው ኤሊቃ፣


በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤ በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።


እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።


እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?


ኢያሱም ማልዶ ተነሣ። ከእስራኤላውያንም ሁሉ ጋራ ከሰጢም ወደ ዮርዳኖስ መጥተው ወንዙን ከመሻገራቸው በፊት በዚያ ሰፈሩ።


ኢያሱ በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፤ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸከሙ።


ስለዚህም፣ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፣ “ይሩባኣል” ብለው ጠሩት።


በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፣ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ኀይላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።


በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደ ተጠየቀው አደረገ፤ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ሲሸፈን፣ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሆነ።


የኢዮአስ ልጅ ይሩባኣል ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።


ከዚያም እግዚአብሔር ይሩባኣልን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ ያለ ሥጋት ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።


ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ሁሉ በአፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ሸለቆ ባለው ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤


跟着我们:

广告


广告