Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 6:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፣ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፥ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፥ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በማግስቱ የከተማይቱ ኗሪዎች ማልደው በተነሡ ጊዜ ለባዓል የተሠራው መሠዊያ መፍረሱንና የአሼራም ምስል ተሰባብሮ መውደቁን አዩ፤ ከዚያም በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ኰርማ ታርዶ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ መቅረቡን ተመለከቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የከ​ተ​ማ​ውም ሰዎች ማል​ደው ተነሡ፤ እነ​ሆም፥ የበ​ዓል መሠ​ዊያ ፈርሶ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ተቈ​ርጦ፥ በተ​ሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ ሁለ​ተ​ኛው በሬ ተሠ​ውቶ አገ​ኙት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የከተማውም ሰዎች ማልደው ተነሡ፥ እነሆም፥ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ፥ በዙሪያው ያለውም የማምለኪያ ዐፀድ ተቈርጦ፥ በተሠራውም መሠዊያ ላይ ሁለተኛው በሬ ተሠውቶ አገኙት።

参见章节 复制




መሳፍንት 6:28
4 交叉引用  

በየኰረብታው ላይ ያሉትን የማምለኪያ ዐምዶች አስወገደ፤ አዕማደ ጣዖታትን ሰባበረ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈራረጠ፤ ሙሴ የሠራውን የናስ እባብ፣ እስራኤላውያን እስከ እነዚያ ጊዜያት ድረስ ዕጣን ያጤሱለት ስለ ነበር ሰባበረው፤ ይህም ነሑሽታን ይባል ነበር።


ጌዴዎን ከአገልጋዮቹ ዐሥር ሰዎች ወስዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተ ሰቡንና የከተማውን ሰው ስለ ፈራ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን ሌሊት ነበር።


እነርሱም፣ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ነገሩን በጥብቅ ሲከታተሉም፣ “የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት።”


ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም መለሰለት።


跟着我们:

广告


广告