Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 6:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጌዴዎን ያየው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ባወቀ ጊዜ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ወዮልኝ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌዴዎን ያየው የጌታ መልአክ መሆኑን ባወቀ ጊዜ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የጌታን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ወዮልኝ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ጌዴዎን ያየው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በተገነዘበ ጊዜ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! የአንተን መልአክ ፊት ለፊት አይቼአለሁ ወዮልኝ!” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ጌዴ​ዎ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴ​ዎ​ንም፥ “አቤቱ! አም​ላኬ ሆይ! ወዮ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ ፊት ለፊት አይ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፥ ጌዴዎንም፦ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወዮልኝ፥ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና አለ።

参见章节 复制




መሳፍንት 6:22
12 交叉引用  

እርሷም ያናገራትን እግዚአብሔርን፣ “ኤልሮኢ” ብላ ጠራችው፤ ምክንያቱም “የሚያየኝን አሁን አየሁት” ብላ ነበርና።


ስለዚህ ያዕቆብ፣ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል፣ የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው።


ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሓይ ወጣችበት፤ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።


ነገር ግን፣ ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል፣ ፊቴን ማየት አትችልም።”


ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው።


ኢሳይያስ ይህን ያለው የኢየሱስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እርሱም ተናገረ።


እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል።


ለመሆኑ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር እኛ እንደ ሰማነው ሁሉ፣ የሕያው እግዚአብሔርን ድምፅ ሰምቶ በሕይወት ለመኖር የቻለ ከሥጋ ለባሽ ማን አለ?


እናንተ ግን እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው ስላልወጣችሁ፣ በዚያ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ለእናንተ እነግራችሁ ዘንድ እኔ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆምሁ። እርሱም እንዲህ አለ፤


እግዚአብሔርም፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ አትሞትም” አለው።


跟着我们:

广告


广告