Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዲቦራ፣ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺሕ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ልካም ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠርታ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፥ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች አሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፥

参见章节 复制




መሳፍንት 4:6
21 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!


ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።


አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤ እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።


ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሡ እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ”። በተራሮች መካከል ያለውን የታቦር ተራራ የሚመስል፣ ባሕርም አጠገብ ያለውን የቀርሜሎስ ተራራ የሚመስል አንድ የሚመጣ አለ።


“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ አድምጡ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።


ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤ “ ‘ድነትን እስከ ምድር ዳርቻ ታደርስ ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ።’ ”


እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ልበል? ስለ ጌዴዎን፣ ስለ ባርቅ፣ ስለ ሳምሶን፣ ስለ ዮፍታሔ፣ ስለ ዳዊት፣ ስለ ሳሙኤል፣ እንዲሁም ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ የለም።


በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”


ድንበራቸውም ታቦርና፣ ሻሕጹማን፣ ቤትሳሚስን ይነካና በዮርዳኖስ ላይ ያቆማል። እነዚህ ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ከተሞች ናቸው።


ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤


የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣


ቃዴስ፣ ኤድራይ፣ ዓይንሐጾር፣


ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤


በዚያም ባርቅ የዛብሎንንና የንፍታሌምን ሰዎች ወደ ቃዴስ ጠራቸው፤ ዐሥር ሺሕ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም ዐብራው ሄደች።


በዚያ ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤


እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፣ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው።


ዛብሄልና ስልማናንም፣ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ሁሉም እንዲህ እንደ አንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት።


“አንተም ጕዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፣ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፣ ሌላው ሦስት ዳቦ፣ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቍማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል።


ከዚያም እግዚአብሔር ይሩባኣልን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ ያለ ሥጋት ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።


跟着我们:

广告


广告