መሳፍንት 21:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በምጽጳ፣ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፣ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በምጽጳ፥ በጌታ ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፥ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በጌታ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 “በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ስንሰበሰብ ወደዚያ ያልመጣ ከእስራኤል ነገዶች መካከል አንድ ወገን እንኳ ይገኛልን?” ብለውም ጠየቁ፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ወደ ምጽጳ ያልሄደ ማንም ሰው ቢገኝ በሞት ለመቅጣት ተማምለው ስለ ነበር ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ስላልወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፥ “ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ስላልወጣ ሰው፦ እርሱ ፈጽሞ ይገደል ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፦ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው? አሉ። 参见章节 |