Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 21:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፣ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፥ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሊጣ​ሉ​አ​ችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩ​አ​ቸው፥ እኛ ሚስት ለያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሰ​ልፍ አል​ወ​ሰ​ድ​ን​ላ​ቸ​ው​ምና፥ እና​ን​ተም በደል ይሆ​ን​ባ​ችሁ ስለ ነበር አላ​ጋ​ባ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምና፥” እን​ላ​ቸ​ዋ​ለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አባቶቻቸውና ወንድሞቻቸውም ሊጣሉአችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩአቸው፥ እኛ ሚስት ለያንዳንዳቸው በሰልፍ አልወሰድንላቸውምና፥ እናንተም በደል ይሆንባችሁ ስለ ነበረ አላጋባችኋቸውምና፥ እንላችኋለን።

参见章节 复制




መሳፍንት 21:22
10 交叉引用  

ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።


በዚያ ዕለት ኖኅና ልጆቹ ሴም፣ ካምና ያፌት፣ እንዲሁም ሚስቱና ሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ወደ መርከቧ ገቡ።


በችኰላ ስእለት መሳል፣ ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው።


ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።


እስራኤላውያን በምጽጳ፣ “ከእኛ አንድም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።


ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።


‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤


ሴቶች ልጆቻችንን ለእነዚህ ብንያማውያን በጋብቻ ላንሰጥ በእግዚአብሔር ስለ ማልን ለተረፉት እንዴት ሚስት ልናገኝላቸው እንችላለን?”


跟着我们:

广告


广告