Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 21:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚ​ያም ጊዜ የብ​ን​ያም ልጆች ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሴቶች ያዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን ሴቶች ሰጡ​አ​ቸው። በዚ​ህም ተስ​ማሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፥ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች አገቡአቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም።

参见章节 复制




መሳፍንት 21:14
7 交叉引用  

ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።


ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ጀርባቸውን አዙረው በምድረ በዳው ውስጥ ወዳለው ወደ ሬሞን ዐለት ሸሹ፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጡ።


በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ወንድ ያልደረሰባቸው አራት መቶ ደናግል አገኙ፤ በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘውም ሰፈር አመጧቸው።


ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ።


እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል አስደንጋጭ ስብራት ስላደረገ ሕዝቡ ለብንያማውያን ዐዘነ።


አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፣ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”


ከዚያም፣ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከኢያቢስ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤


跟着我们:

广告


广告