መሳፍንት 20:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ብንያማውያኑ፣ “እንደ በፊቱ ይኸው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፣ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፣ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማዪቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ብንያማውያንም “ልክ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ፈጀናቸው” አሉ። እስራኤላውያን ግን “ወደ ኋላ አፈግፍገን ከከተማው ወደ አውራ ጐዳናው እናስወጣቸው” አሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 የብንያምም ልጆች፥ “እንደ ቀድሞው በፊታችን ይሞታሉ” አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፥ “እንሽሽ፤ ከከተማም ወደ መንገድ እናርቃቸው” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 የብንያምም ልጆች፦ እንደ ቀድሞው በፊታችን ተመቱ አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፦ እንሽሽ፥ ከከተማም ወደ መንገድ እንሳባቸው አሉ። 参见章节 |