Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋራ ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፣ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ ዕደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ ዐድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጧት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፥ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ እደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ አድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጠዋት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሌዋዊውና ቊባቱ እንዲሁም አገልጋዩ ሆነው እንደገና ጒዞ ሲጀምሩ የልጅቱ አባት እንዲህ አለ፤ “ተመልከቱ! እነሆ ጊዜው መሽቶአል፤ ሌሊቱን እዚሁ ብታሳልፉ ይሻላል፤ አሁን ፈጥኖ ይጨልማል፤ እዚሁ ደስ ብሎአችሁ ዕደሩ፤ ነገ በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞ በመጀመር ወደ ቤታችሁ ትሄዳላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሰው​ዬ​ውም ከዕ​ቅ​ብ​ቱና ከብ​ላ​ቴ​ናው ጋር ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት አማ​ቱም፥ “እነሆ፥ መሽ​ት​ዋል፤ ፀሐ​ዩም ሊጠ​ልቅ ደር​ሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚ​ህም ተቀ​መጥ፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ለው፤ በጥ​ዋ​ትም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ወደ ቤት​ህም ትገ​ባ​ለህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰውዮውም ከቁባቱና ከአሽከሩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ የብላቴናይቱ አባት አማቱ፦ እነሆ፥ ቀኑ ተዋግዶአል፥ በዚህ እደሩ፥ እነሆ፥ ቀኑ ለማለፍ ተዋግዶአል፥ ልባችሁ ደስ እንዲለው በዚህ እደሩ፥ ነገም ወደ ቤታችሁ እንድትደርሱ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:9
8 交叉引用  

አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።


ነገ በሚሆነው አትመካ፤ ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና።


እነርሱ ግን፣ “ምሽት እየተቃረበ፣ ቀኑም እየተገባደደ ስለ ሆነ ከእኛ ጋራ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለማደር ገባ።


ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ።


ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት ዐብረው ተቀመጡ። የልጅቷም አባት፣ “እባክህ ዛሬም እዚሁ ዐድረህ ተደሰት” አለው።


በዐምስተኛውም ቀን ጧት ሌዋዊው ለመሄድ ሲነሣ፣ የልጅቱ አባት “ሰውነትህን አበርታ፤ ጥላው እስኪበርድም ድረስ በዚሁ ቈይ” አለው፤ ስለዚህ ሁለቱም ዐብረው በሉ።


ቦዔዝ በልቶ ጠጥቶ ከጨረሰና ደስም ከተሠኘ በኋላ፣ ራቅ ካለው የእህል ክምር አጠገብ ለመተኛት ሄደ። ሩት በቀስታ ከአጠገቡ ደረሰች፤ እግሩንም ገልጣ ተኛች።


跟着我们:

广告


广告