Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሽማግሌውም፣ “ኑ ግቡ በቤቴም ዕደሩ፤ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አቀርባለሁ፤ በአደባባይ ግን አትደሩ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሽማግሌውም፥ “ኑ ግቡ በቤቴም እደሩ፤ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አቀርባለሁ፤ በዐደ ባባይ ግን አትደሩ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሽማግሌውም “ሰላም ለአንተ ይሁን! እነሆ ወደ ቤቴ ግባ! እኔ ማደሪያ አዘጋጅልሃለሁ፤ በዚህ አደባባይ ላይ ማደር አይገባህም” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሽማ​ግ​ሌ​ውም ሰው፥ “ሰላም ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ የም​ት​ሻ​ው​ንም ሁሉ እኔ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ በአ​ደ​ባ​ባይ ግን አት​ደር” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሽማግሌውም፦ ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን፥ የምትሻውንም ሁሉ እኔ እሰጥሃለሁ፥ በአደባባይ ግን አትደር አለው።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:20
15 交叉引用  

ከዚያም መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “ዳዊት ሆይ፤ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፤ እኛ ከአንተ ጋራ ነን፤ ሰላም ፍጹም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤ አምላክህ ይረዳሃልና።” ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ የሰራዊቱም አለቃ አደረጋቸው።


ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።


ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋራ ይካፈል።


እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ፣ ሳያውቁ መላእክትን አስተናግደዋልና።


እርስ በርሳችሁ ያለ ማጕረምረም እንግድነት ተቀባበሉ።


ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።


እግዚአብሔርም፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ አትሞትም” አለው።


እንዲህም በሉት፤ ‘ዕድሜህ ይርዘም! ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተ ሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።


跟着我们:

广告


广告