Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሌዋዊው ግን ያንን ሌሊት እዚያ ለማሳለፍ አልፈለገም፤ ስለዚህ እርሱ፥ ቊባቱና አገልጋዩ ተነሥተው ጒዞ ጀመሩ፤ ኮርቻ የተጫኑ ሁለት አህዮችም ነበሩአቸው፤ ቀኑም በመሸ ጊዜ የቡስ ተብላ ትጠራ ወደነበረችው ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ አጠገብ ደረሱ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሰው​ዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማ​ደር አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወደ ተባ​ለ​ችው ወደ ኢያ​ቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት የተ​ጫኑ አህ​ዮች ነበሩ፤ ዕቅ​ብ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰውዮው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፥ ተነሥቶም ሄደ፥ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለች ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፥ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:10
7 交叉引用  

ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ሄዱ። ኢያቡሳውያንም፣ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፣ “ዕውሮችና ዐንካሶች እንኳ ይከለክሉሃልና ወደዚህች አትገባም” አሉት።


ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋራ በኢየሩሳሌም ዐብረው ይኖራሉ።


እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል።


ጼላ ኤሌፍ፣ የኢያቡሳውያን ከተማ ኢየሩሳሌም፣ ጊብዓ እንዲሁም ቂርያት ነበሩ፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ከተሞች ናቸው። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየጐሣቸው የወረሱት ይህ ነበር።


የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት መተው፣ በእሳት አቃጠሏት።


ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋራ ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፣ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ ዕደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ ዐድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጧት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告