Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ ዐምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ሥጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፣ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለመኖሩ ሕዝቡ ባለጠጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋራ ግንኙነት አልነበረውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ሄደው ወደ ላዪሽ ደረሱ፤ በዚያም የነበሩት ኗሪዎች ልክ እንደ ሲዶናውያን በሰላም የሚኖሩ መሆናቸውን ተመለከቱ፤ ሕዝቡም ከማንም ጋር ሳይጋጩ ጸጥ ባለ መንፈስ የሚኖሩ ሰላም ወዳዶች ነበሩ፤ ከዚህም ጋር ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም የሚጐድላቸው አልነበረም፤ ከዚህም የተነሣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከሲዶናውያን በመራቅ ተገልለው ይኖሩ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አም​ስ​ቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በው​ስ​ጡም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ተዘ​ል​ለው አዩ​አ​ቸው፤ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐር​ፈው፥ ተዘ​ል​ለ​ውም ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ በተ​መ​ዘ​ገ​በች የር​ስ​ታ​ቸው ምድ​ርም ቃልን መና​ገር አል​ቻ​ሉም፤ ከሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አምስቱም ሰዎች ሄዱ ወደ ሌሳም መጡ፥ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፥ አንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው ተዘልለው ተቀምጠው ነበር፥ የሚያስቸግራቸውም የሚገዛቸውም አልነበረም፥ ከሲዶናውያንም ርቀው ከሰውም ሁሉ ተለይተው ለብቻቸው ይኖሩ ነበር።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:7
13 交叉引用  

አባቱም፣ “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ ገሥጾት አያውቅም ነበር፤ አዶንያስም እጅግ መልከ መልካምና የአቤሴሎም ታናሽ ወንድም ነበር።


የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት እንደ ቀላል ነገር ከመቍጠሩም በላይ የሲዶናውያንን ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።


በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው።


“ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣ በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።


ገዦች ክፉ ለሚሠሩ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያስ መልካሙን አድርግ፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤


ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።


ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣትና በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤


ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤ በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ከቶም አላዝንም፤’


ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት፤ ቀድሞ ግን ስሟ ላይሽ ይባል ነበር።


ካህኑም፣ “በሰላም ሂዱ፤ መንገዳችሁን እግዚአብሔር አቃንቶላችኋል” ብሎ መለሰላቸው።


ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደ ተመለሱ ወገኖቻቸው፣ “የሄዳችሁበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው።


ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም።


跟着我们:

广告


广告