Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነርሱም፣ “ዝም በል! አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋራ ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተ ሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነርሱም፥ “ዝም በል አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነርሱም “ዝም በል! አፍህን ዝጋ፤ ይልቅስ መጥተህ ካህናችንና አማካሪያችን ሁን፤ የአንድ ሰው ቤተሰብ ካህን ከምትሆን የአንድ እስራኤላዊ ነገድ ካህን መሆን አይሻልህምን?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ር​ሱም፥ “ዝም በል፤ እጅ​ህ​ንም በአ​ፍህ ላይ ጫን፤ ከእ​ኛም ጋር ና፥ አባ​ትና ካህ​ንም ሁን​ልን፤ ለአ​ንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለነ​ገ​ድና ለወ​ገን ካህን መሆን ማና​ቸው ይሻ​ል​ሃል?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነርሱም፦ ዝም በል፥ እጅህንም በአፍህ ላይ ጫን፥ ከእኛም ጋር መጥተህ አባትና ካህን ሁንልን፥ ለአንድ ሰው ቤት መሆን ወይስ በእስራኤል ዘንድ ለነገድና ለወገን ካህን መሆን ማናቸው ይሻልሃል? አሉት።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:19
12 交叉引用  

በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።


የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ፣ “አባቴ ሆይ፤ ልግደላቸውን? ልፍጃቸውን?” ብሎ ኤልሳዕን ጠየቀው።


ተመልከቱኝና ተገረሙ፤ አፋችሁን በእጃችሁ ለጕሙ።


የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤


“ተላላ ሆነህ ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግህ፣ ወይም ክፉ ነገር ካቀድህ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።


አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ ጆሯቸውም ትደነቍራለች።


በሰማይ ያለ አንድ አባት ስላላችሁ፣ በምድር ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።


ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።


እነዚህ ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በሚወስዱበት ጊዜ ካህኑ፣ “ምን ማድረጋችሁ ነው?” አላቸው።


ይህም ካህኑን ደስ አሠኘው፤ እርሱም ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውን ምስል ይዞ ከሕዝቡ ጋራ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告