መሳፍንት 16:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ። አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ከዚህ በኋላ ሶምሶን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አስበኝ፤ አምላኬ ሆይ! እባክህ ኀይል ስጠኝና ፍልስጥኤማውያን ዐይኖቼን ስላወጡ አንድ ጊዜ ብቻ እንድበቀላቸው አድርገኝ!” ብሎ ጸለየ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ሶምሶንም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስበኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበርታኝ፤ እንግዲህ ስለ ሁለቱ ዐይኖቼ ፋንታ ከፍልስጥኤማውያን አንዲት በቀልን እበቀላለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ሶምሶንም፦ ስለ ሁለቱ ዓይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አሁን እንድበቀል፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እባክህ፥ አስበኝ፥ አምላክ ሆይ፥ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ፥ እባክህ፥ አበርታኝ ብሎ እግዚአብሔርን ጠራ። 参见章节 |