Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ይዘው ዐይ​ኖ​ቹን አወ​ጡት፤ ወደ ጋዛም አው​ር​ደው በእ​ግር ብረት አሰ​ሩት፤ በግ​ዞ​ትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፥ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፥ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:21
15 交叉引用  

ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየም ወንዶች ልጆቹን ገደሉበት፤ ከዚያም ሁለት ዐይኖቹን በማውጣት በናስ ሰንሰለት አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣ መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤


በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን ልጅ አንሥቶ የወፍጮ መጅ ገፊ እስከ ሆነችው እስከ ባሪያዪቱ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኵር ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የቀንድ ከብቱ በኵር በሙሉ ያልቃል።


ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።


ወደ እርሷ የሚገባ ማንም አይመለስም፤ የሕይወትንም መንገድ አያገኝም።


ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤ የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል።


ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤ መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽንም ከፍ ከፍ አድርጊ፤ ባትሽን ግለጪ፤ እየተንገዳገድሽ ወንዙን ተሻገሪ።


የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ ወደ ባቢሎን ሊወስደውም በናስ ሰንሰለት አሰረው።


ጕልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።


ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!”


ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፣ ሌላዋ ትቀራለች።


እርሷም፣ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም ነበር።


ነገር ግን ከተላጨ በኋላ ጠጕሩ እንደ ገና ማደግ ጀመረ።


跟着我们:

广告


广告