መሳፍንት 16:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ደሊላ፣ ሳምሶንን በጭኗ ላይ አስተኝታ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገች በኋላ አንድ ሰው ጠርታ ሰባቱን የጠጕር ሹሩባዎቹን አስላጨቻቸው፤ እርሷም ታስጨንቀው ጀመር፤ ኀይሉም ተለየው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ደሊላ፥ ሳምሶንን በጭኗ ላይ አስተኝታ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገች በኋላ አንድ ሰው ጠርታ ሰባቱን የጠጉር ቈንዳላዎቹን አስላጨቻቸው፤ እርሷም ታስጨንቀው ጀመር፤ ኃይሉም ተለየው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ደሊላ ሶምሶንን በጭንዋ ላይ አስተኝታ፤ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገች። አንድ ሰውም ጠርታ ሰባቱን የጠጒሩን ቁንዳላዎች እንዲቈረጡ አደረገች፤ ኀይሉም ከእርሱ ተለይቶት ስለ ነበር በማዋረድ ታስጨንቀው ነበር፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እርስዋም በጕልበቷ ላይ አስተኛችው፤ ጠጕር ቈራጭም ጠራች፤ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ይደክምም ጀመረ፤ ኀይሉም ከእርሱ ሄደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እርስዋም በጉልበትዋ ላይ አስተኛችው፥ አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጉንጉን ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ። 参见章节 |