Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ ሁሉንም ነገር ነገራት፤ እንዲህም አለ፤ “ከተወለድሁ ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆንሁ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም፤ የራሴ ጠጕር ቢላጭ ግን ኀይሌ ተለይቶኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለዚህ ሁሉንም ነገር ነገራት፤ እንዲህም አለ፤ “ከተወለድሁ ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆንኩ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም፤ የራሴ ጠጉር ቢላጭ ግን ኃይሌ ተለይቶኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በመጨረሻ እውነቱን ነገራት፤ እንዲህም አላት፦ “ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆነ ጠጒሬ ተላጭቶ አያውቅም፤ ጠጒሬ ቢላጭ ግን ኀይል ተለይቶኝ እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ሱም፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናዝ​ራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አል​ነ​ካ​ኝም፤ የራ​ሴ​ንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነ​ሣል፤ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ የል​ቡን ሁሉ ነገ​ራት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም፦ ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም፥ የራሴንም ጠጉር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፥ እደማክለሁም፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:17
10 交叉引用  

አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤ የሞኞች ልብ ግን ቂልነትን ይነዛል።


አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።


ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።


ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።


“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ ‘ወንድም ሆነ ሴት ናዝራዊ ይሆን ዘንድ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመለየት ስእለት ቢሳል፣


“ ‘ስእለት ተስሎ ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ምላጭ ራሱን አይንካው፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የተቀደሰ ይሁን፤ የራስ ጠጕሩንም ያሳድግ።


ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ብዙ ቀን በቆሮንቶስ ተቀመጠ፤ ከዚያም ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋራ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለትም ስለ ነበረበት ክንክራኦስ በተባለ ቦታ ራሱን ተላጨ።


ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለአምላክ የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።”


በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው።


ደሊላ ሁሉንም ነገር እንደ ነገራት በተረዳች ጊዜ፣ ለፍልስጥኤማውያን ገዦች “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና ተመልሳችሁ ኑ” ብላ ላከችባቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም ብሩን ይዘው ተመልሰው መጡ።


跟着我们:

广告


广告