Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም፣ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኀይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያም፥ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኃይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ እርስዋ “ልብህ ከእኔ ጋር ሳይሆን እንዴት እወድሻለሁ ትለኛለህ? ሦስት ጊዜ አታለልከኝ፤ እስከ አሁንም ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘኸው ከምን እንደ ሆነ አልነገርከኝም” አለችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ደሊ​ላም፥ “ ‘አንተ እወ​ድ​ድ​ሻ​ለሁ’ እን​ዴት ትለ​ኛ​ለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይ​ደ​ለም፤ ስታ​ታ​ል​ለኝ ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይ​ል​ህም በምን እንደ ሆነ አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም” አለ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርስዋም፦ አንተ፦ እወድድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:15
18 交叉引用  

ያዕቆብም ራሔልን ለማግኘት ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ለርሷ ካለው ፍቅር የተነሣ፣ ሰባት ዓመት እንደ ጥቂት ቀን ሆኖ ታየው።


አቤሴሎምም፣ ኩሲን፣ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት እስከዚህ ድረስ ነው? ለምን ከወዳጅህ ጋራ አልሄድህም?” ሲል ጠየቀው።


አራት ጊዜም ይህንኑ ዐይነት መልእክት ላኩብኝ፤ እኔም በእያንዳንዱ ጊዜ ያንኑ መልስ ሰጠሁ።


ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤ በአንደበቷም ከምታታልል ባዕድ ታድንሃለች፤


ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤


“ብትወድዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።


አንተም እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።


እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዞቹን መፈጸም ነውና። ትእዛዞቹም ከባድ አይደሉም፤


ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፣ “ለካስ ትጠላኛለህ! በርግጥ አትወድደኝም” አለችው። እርሱም፣ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት።


ከችካልም ጋራ ቸከለችው። እንደ ገናም፣ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፣ ከነሹሩባው ነቀለው።


በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው።


跟着我们:

广告


广告