Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከችካልም ጋራ ቸከለችው። እንደ ገናም፣ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፣ ከነሹሩባው ነቀለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ቈንዳላዎቹን ከድር ጋር ጐነጐነችው፤ ከችካልም ጋር ቸከለችው። እንደገናም፥ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፥ ከነቈንዳላው ነቀለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ ደሊላ ተኝቶ ሳለ የራሱን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጒና በችካል ቸከለችው፤ ከዚያ በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች፤ እርሱ ግን ከእንቅልፉ ነቅቶ ጠጒሩን ከችካሉና ከድሩ ላይ ነቀለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደሊ​ላም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ጐነ​ጐ​ነ​ችው፤ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ቸከ​ለ​ቻ​ቸው፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቃ፥ ችካ​ሉ​ንም ከነ​ቈ​ን​ዳ​ላው ከግ​ድ​ግ​ዳው ነቀለ፤ ኀይ​ሉም አል​ታ​ወ​ቀም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሶምሶንም በተኛ ጊዜ ደሊላ የራሱን ጠጉር ሰባቱን ጉንጉን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፥ በችካልም ቸከለችውና፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቃ፥ ችካሉንም ከነቆንዳላው ድሩንም ነቀለ።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:14
4 交叉引用  

እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤ በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።


ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፣ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደ ሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፣ “የራስ ጠጕሬን ሰባት ሹሩባዎች ከድር ጋራ ጐንጕነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ሹሩባዎቹን ከድር ጋራ ጐነጐነችው፤


ከዚያም፣ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኀይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።


跟着我们:

广告


广告