Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ደሊላም አዳዲስ ገመዶች ወስዳ አሰረችው፤ ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፣ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱ ግን ክንዱ የታሰረባቸውን ገመዶች እንደ ፈትል ክር በጣጠሳቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ደሊላም አዳዲስ ገመዶች ወስዳ አሰረችው፤ ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፥ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱ ግን ክንዱ የታሰረባቸውን ገመዶች እንደ ፈትል ክር በጣጠሳቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ አሰረችው፤ በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ገመዱን ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ደሊ​ላም ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ወስዳ በእ​ነ​ርሱ አሰ​ረ​ችው፤ የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተቀ​ም​ጠው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ገመ​ዶ​ች​ንም ከክ​ንዱ እንደ ፈትል በጣ​ጠ​ሳ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ በእርሱ አሰረችው፥ በጓዳዋም የተደበቁ ሰዎች ተቀምጠው ነበር። እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ገመዱንም ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:12
4 交叉引用  

የጦር አዛዡም ቀርቦ ያዘው፤ በሁለት ሰንሰለትም እንዲታሰር ትእዛዝ ሰጠ፤ ከዚያም ማን መሆኑንና ምን እንዳደረገ ጠየቀ።


ሳምሶን ሌሒ እንደ ደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ።


እርሱም፣ “ሥራ ላይ ባልዋሉ አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።


ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፣ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደ ሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፣ “የራስ ጠጕሬን ሰባት ሹሩባዎች ከድር ጋራ ጐንጕነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ሹሩባዎቹን ከድር ጋራ ጐነጐነችው፤


跟着我们:

广告


广告