Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 15:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋር አሰረው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሄዶም ሦስት መቶ ቀበሮዎችን በማደን ያዘ፤ ጥንድ ጥንድ አድርጎ ጭራቸውን በማያያዝ በገመድ አሰረ፤ ችቦዎችም አምጥቶ በጭራቸው መካከል አሰረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፥ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፥ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ።

参见章节 复制




መሳፍንት 15:4
8 交叉引用  

ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ የኢዮአብ ዕርሻ የሚገኘው ከእኔ ዕርሻ አጠገብ ነው፤ በዕርሻው ላይ የገብስ አዝመራ አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው የኢዮአብን ዕርሻ በእሳት አቃጠሉት።


ለሰይፍ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።


ትንታግ ወይም የሚገድል ፍላጻ እንደሚወረውር እብድ፣


የወይን ተክሉን ቦታ፣ በማበብ ላይ ያለውን የወይን ተክል ቦታችንን፣ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ እነዚያን ትንንሽ ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙልን።


እንዲህም በለው፤ ‘ተጠንቀቅ፤ ተረጋጋ፤ አትፍራ፤ በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱት በሁለቱ የዕንጨት ጕማጆች፣ በሶርያና በንጉሥዋ በረአሶን እንዲሁም በሮሜልዩ ልጅ ቍጣ አትሸበር።


ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣ የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።


ሳምሶንም መልሶ፣ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጕዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው።


ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ።


跟着我们:

广告


广告