Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 13:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለአምላክ የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በእርግጥ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የራስ ጠጒሩን ፈጽሞ አይላጭ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፥ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።

参见章节 复制




መሳፍንት 13:5
9 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።


ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል መትቶ ተገዥ አደረጋቸው፤ ጋትንና በዙሪያዋም የሚገኙትን መንደሮች ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።


“ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣ ናዝራውያንንም ከጕልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።


“ ‘ስእለት ተስሎ ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ምላጭ ራሱን አይንካው፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የተቀደሰ ይሁን፤ የራስ ጠጕሩንም ያሳድግ።


በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ በእናቱም ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል።


ስለዚህ ሁሉንም ነገር ነገራት፤ እንዲህም አለ፤ “ከተወለድሁ ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆንሁ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም፤ የራሴ ጠጕር ቢላጭ ግን ኀይሌ ተለይቶኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።


እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።”


በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።


跟着我们:

广告


广告