Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 12:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ እግዚአብሔርም ድሉን ሰጠኝ። ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እናንተ እኔን ለመርዳት አለመፈለጋችሁን ባየሁ ጊዜ ለሕይወቴ ሳልሳሳ እነርሱን ለመውጋት ወሰኑን ተሻግሬ ሄድሁ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኝ። ታዲያ፥ አሁን እኔን ለመውጋት የተነሣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሚ​ያ​ድን እን​ደ​ሌ​ለም ባየሁ ጊዜ ሰው​ነ​ቴን በእጄ አሳ​ልፌ ለሞት በመ​ስ​ጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገ​ርሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቴ ጣላ​ቸው፤ ለም​ንስ ዛሬ ልት​ወ​ጉኝ ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዳላዳናችሁኝም ባየሁ ጊዜ ነፍሴን በእጄ አድርጌ በአሞን ልጆች ላይ አለፍሁ፥ እግዚአብሔርም በእጄ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ለምንስ ዛሬ ልትወጉኝ ወደ እኔ መጣችሁ? አላቸው።

参见章节 复制




መሳፍንት 12:3
11 交叉引用  

እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ መሪያችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ አትዋጉ።”


ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?


ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።


እነርሱም ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሰጡ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል።


እነርሱም በበጉ ደም፣ በምስክርነታቸውም ቃል፣ ድል ነሡት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ፣ ለነፍሳቸው አልሳሱም።


እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጁ እግዚአብሔር በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።”


ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋራ ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤


ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋራ ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፣ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው።


አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፣ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን ዐሰባችሁ ማለት ነው።


ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቈርጦ ነው። እግዚአብሔር ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”


ሴትዮዋ ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መደንገጡን ባየች ጊዜ እንዲህ አለችው፤ “እነሆ፤ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ በነፍሴም ቈርጬ የነገርኸኝን ፈጽሜአለሁ።


跟着我们:

广告


广告