Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 10:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እንዲሁም አሞናውያን ይሁዳን፣ ብንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ስለ ተሻገሩ እስራኤላውያን እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የአሞንም ልጆች ከይሁዳ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጋ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዐሞናውያን የይሁዳን፥ የብንያምንና የኤፍሬምን ነገዶች ለመውጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የአ​ሞ​ንም ልጆች ከይ​ሁዳ፥ ከብ​ን​ያ​ምና ከኤ​ፍ​ሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እጅግ ተጨ​ነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የአሞንም ልጆች ከይሁዳ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጋ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ።

参见章节 复制




መሳፍንት 10:9
13 交叉引用  

ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰራዊትና ሦስት መቶ ሠረገላ ይዞ በመውጣት እስከ መሪሳ ድረስ መጣባቸው።


በዚያ ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም።


በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፣ በናፍቆት የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቈርጥ ልብ ይሰጥሃል።


ከዚያም እስራኤላውያን፣ “አንተን አምላካችንን በመተው የበኣልን አማልክት በማምለካችን አንተን በድለናል” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።


እነርሱም በዚያ ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ ለዐሥራ ስምንት ዓመታት ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው የአሞራውያን ምድር፣ በገለዓድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ሁሉ አሠቃዩአቸው።


ከጥቂት ጊዜ በኋላም አሞናውያን በእስራኤል ላይ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ፣


እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረውና እንደ ማለው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።


እስራኤላውያን የምድያማውያን ኀይል ስለ በረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፣ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።


እስራኤላውያን፣ ያሉበት ሁኔታ እጅግ የሚያሠጋ መሆኑንና ሰራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፣ በየዋሻውና በየእሾኽ ቍጥቋጦው፣ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጕድጓዱ ሁሉ ተደበቁ።


ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድን ነው?” አለው። ሳኦልም፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው።


跟着我们:

广告


广告