Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 10:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱም በዚያ ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ ለዐሥራ ስምንት ዓመታት ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው የአሞራውያን ምድር፣ በገለዓድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ሁሉ አሠቃዩአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አሞናውያንና ፍልስጥኤማውያንም ከዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የሚኖሩትን እስራኤላውያንን ለዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨንቀው ገዙአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥቃይ አበ​ዙ​ባ​ቸው፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ያሉ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።

参见章节 复制




መሳፍንት 10:8
7 交叉引用  

ስለዚህ ይህ ኀጢአት፣ ተሰነጣጥቆ ሊወድቅ እንደ ደረሰ፣ ሳይታሰብ ድንገት እንደሚወድቅ ረዥም ቅጥር ይሆንባችኋል።


የምናሴ ልጅ የሆነው የማኪር ዘሮች ወደ ገለዓድ ሄደው ምድሪቱን በመያዝ፣ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አሳደዷቸው፤


ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


ኢያዕር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።


እግዚአብሔርም ተቈጣቸው፤ በፍልስጥኤማውያንና በአሞናውያን እጅ ሸጣቸው፤


እንዲሁም አሞናውያን ይሁዳን፣ ብንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ስለ ተሻገሩ እስራኤላውያን እጅግ ተጨነቁ።


እስራኤላውያን የምድያማውያን ኀይል ስለ በረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፣ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።


跟着我们:

广告


广告