Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 8:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ያደፈጠው ጦር ከተማዪቱን መያዙንና ጢሱ ወደ ላይ መውጣቱን ሲያዩ፣ ወደ ኋላ ተመልሰው በጋይ ሰዎች ላይ አደጋ ጣሉባቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማይቱን እንደ ያዙ፥ የከተማይቱም ጢስ ወደ ላይ እንደ ጤሰ ባዩ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢያሱና ከእርሱ ጋር ተሰልፎ የነበረው ሠራዊት ቀደም ብለው ያዘጋጁት ሽምቅ ጦር ከተማይቱን በቊጥጥር ሥር ማድረጉንና በእሳት ማቃጠሉን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለው የዐይን ሰዎች መቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢያሱ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩት ከተ​ማ​ዪ​ቱን እንደ ያዙ፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደ​ኋላ ተመ​ል​ሰው የጋ​ይን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማይቱን እንደ ያዙ፥ የከተማይቱም ጢስ እንደ ተነሣ ባዩ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 8:21
4 交叉引用  

ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል ጀግንነታቸው ከታወቀው ጥቂቶቹን መርጦ በሶርያውያን ግንባር አሰለፋቸው።


የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን ይዞ እንደ ደመሰሳት፣ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ማድረጉን፣ የገባዖን ሰዎችም ከእስራኤል ጋራ የሰላም ውል አድርገው በአጠገባቸው መኖራቸውን ሰማ።


የጋይ ሰዎች ወደ ኋላ ዞረው ሲመለከቱ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሸሹ የነበሩት እስራኤላውያን ፊታቸውን ስላዞሩባቸውም፣ በየትኛውም በኩል ማምለጫ መንገድ አልነበራቸውም።


ያደፈጡትም ሰዎች እንደዚሁ ከከተማዪቱ ወጥተው መጡባቸው። ስለዚህ እስራኤላውያን በዚያም በዚህም ስለ ከበቧቸው የጋይን ሰዎች ከመካከል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም ሰዎቹን ፈጇቸው፤ አንድ እንኳ የተረፈ ወይም ያመለጠ አልነበረም፤


跟着我们:

广告


广告