Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 4:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እስራኤላውያንም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረውም መሠረት፣ በእስራኤል ነገዶች ቍጥር ልክ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል አነሡ፤ ወደ ሰፈራቸውም ይዘው በመሻገር በዚያ አኖሯቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፤ ጌታም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቍጥር ከዮርዳኖስ መካከል ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰዎቹም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረው መሠረት በእስራኤል ነገዶች ቊጥር ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወደ ሰፈሩበት ቦታ ወስደው አስቀመጡ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢያሱ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዮር​ዳ​ኖ​ስን አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እንደ አዘ​ዘው በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ቍጥር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮች አን​ሥ​ተው ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወሰዱ፤ በዚ​ያም አኖ​ሩ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፥ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 4:8
6 交叉引用  

እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።


ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግስቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።


ኢያሱም ከዮርዳኖስ ወንዝ ያወጧቸውን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች በጌልገላ ተከላቸው፤


ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ቆመውበት በነበረው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚሁ ስፍራ ይገኛሉ።


跟着我们:

广告


广告